የወር አበባ


የወር አበባ ብዙ እህቶቻችን በተደጋጋሚ የጠየቁን ጥያቄ ነው
።።።።።።።።።።Share share share።።።።።።።።።።
- በወር አበባ ጊዜ መስቀል መሳለም፣ መጽሐፍ ቅዱስ እና ሌሎች ጸሎት መጽሀፍትን ማንበብ ይቻላል? እንዲሁም ወደ ቤተክርስትያን መሄድ ይቻላል ? የወር አበባ በሴቶች ላይ በየወሩ የሚታይ የደም መፍሰስ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮደመ ጽጌ፣ አበባ ደምበመባል ይጠራል፡፡አሰያየሙም የወንድ ዘር ካላገኘ ከማህጸን ግድግዳ ፍራሽ ጋር በደም መልክ ስለሚፈስና የኋለኛው ማንነቱ ደምነት ስለሆነ ነው፡፡ ይህም ማለት አገልግሎቱን የጨረሰ፣ ያረጀ፣ ቆሻሻ ማለት ነው፡፡ ይህ በየወሩ ዑደትን ተከትሎ የሚሄደው የዘር ፍሳሽ በስነ ህይወት ትምህርት ኦቫሪ (ከዘር ከረጢት) የሚለቀቅ የወንድ ዘር ካላገኘ ኦቫ (ሴቴ ዘር) ጋር እየተቀላቀለ የሚወርድ ነው፡፡ የወር አበባ በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ በሁለት ከፍለን ነው መመልከት ያለብን፤ በዘመነ ኦሪትና ዘመነ አዲስ ኪዳን በማለት፡፡ በርግጥ በዘመነ ኦሪት የወር አበባ የርኩሰትና የመርገም ምልክት ነበር፡፡ ለዚህም ማስረጃነት በመጽሃፍ ቅዱስ ዘሌ 18÷19 20÷18 ያሉ ጥቅሶችበመርገምዋ ርኩሰት ሳለችእናባለ መርገም ሴትበማለት ሲገልጸው፤ ባንጻሩ ደግሞ ከወር አበባዋ ነጻ የሆነችውን ሴትከርኩሰትዋ ነጽታበማለት የወር አበባ የርኩሰትና የመርገም ምልክት መሆኑን ይጠቁማል፡፡ በዘመነ አዲስ ደግሞ የወር አበባ የርኩሰትና የመርገም ምልክት መሆኑ ቀርቷል፡፡ ርኩሰት አይደለም፤ ርኩስም አያሰኝም፡፡ በብሉይ ኪዳን አዳምና ሄዋን በገነት በነበሩ ጊዜ ዕጸ በለስን በልተው እግዚአብሔርን በደሉ፤ እግዚአብሔርም ሄዋንን ደመ ዕጸ በለስን አፍስሰሻልናወበከመ አድመውኪያ ለእንትኩ ዕጽ ከማሁ ድምዊ ለለወርኁ፡፡በማለት ደሟ በየወሩ እንዲፈስ ፈጣሪ ፈረደባት፡፡ ስለዚህ የሄዋን ደም መፍሰስ መነሻው መርገም ነው፡፡ በአዲስ ኪዳን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሥቶስ በፈጸመው ቤዛነት መርገምነቱና ርኩስነቱ ተወግዷል፡፡ የወር አበባ በዚህ ዘመን ርኩሰት ወይም መርገም ባይሆንም እድፍ (ቆሻሻ) ነው፡፡ እድፍና ርኩሰት ልዩነት አላቸው፡፡ ርኩሰት ውስጣዊ ነው፤ በንስሃ እንጂ በውሃ አይጠራም፡፡ እድፍ ደግሞ ግዘፍ አካል ያለው፣ የሚታይና ውሃ የሚያነጻው ነው፡፡ የወር አበባ በሴቶች ባህሪ ሳለ እንደ ቆሻሻ አይቆጠርም፣ ከሰውነት ሲወገድ ግን ይቆጠራል፡፡ ይህንን ለማስረዳት ምሳሌ መሆን ከሚችሉት ውስጥ ዛህል (ንፍጥ) ሽንት፣ ምራቅ፣ ዓይነምድርና ሌሎችንም መጥቀስ ይቻላል፡፡ ወር አበባ ርኩሰት ባለመሆኑ መስቀል ከመሳም፣ ከመጸለይ፣ ቅዱሳት መጻህፍትን ከማንበብና ከመድገም አያግድም፡፡ ነገር ግን ከሩካቤ፣ ከመጠመቅ፣ ከመቁረብና ቤተ መቅደስ ከመግባት ይከለክላል፡፡ ከሩካቤ:- ሩካቤ በወር አበባ ጊዜ ከሚከለከሉ ነገሮች አንዱ ነው፡፡ በወር አበባ ጊዜ የሚደረግ ግንኙነት የህክምና ባለሙያዎች ሳይቀር ለአባላዘር፣ ለልዩ ልዩ በሽታዎችና ለኢንፌክሽን ሊያጋልጥ እንደሚችል በመናገር እንዳይፈጸም ይመክራሉ፡፡ በመንፈሳዊው አስተምህሮ ስንመለከተው ደግሞ የሰው ልጅ ዘር ቅዱስ በሆነው በእግዚአብሔር አምሳል በመፈጠሩ፣ ይህንን የተከበረ ዘር፣ እዳሪ ወይም ቆሻሻ ከሆነ ደም ጋር ማዋሃድ ኃጢያት እንደሆነ ይቆጠራል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ሴት ልጅ በወር አበባዋ ጊዜ እንዳለች የሚፈጸምን ሩካቤእርሷም በመርገምዋ ርኩሰት ሳለች ኃፍረተ ሥጋዋን ትገልጥ ዘንድ ወደ እርሷ አትቅረብዘሌ 18÷19 ዘሌ 20÷18 በዚህም ምክንያት በወር አበባ ጊዜ የሚፈጸም ሩካቤ በኦሪትም ይሁን በአዲስ ኪዳን ክልክል ነው፡፡ ከመጠመቅ:- ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌ ሆኖ አሁን ያድነናል፤ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም፡፡ ለእግዚአብሔር በጎ ህሊና ልመና ነው እንጂ” 1 ጴጥ 3÷21 በማለት ተናግሯል፡፡ ስለዚህ ጥምቀት ስጋዊ እድፍን ማስወገጃ ስላልሆነ፣ ከመጠመቅ በፊት ተጣጥበው እንጂ ከእድፍ ጋር ለመጠመቅ መቅረብ ተገቢ አይደለም፡፡ የወር አበባም ከላይ እንደተመለከተው ከሰውነት ሲወጣ እድፍ (ቆሻሻ) በመሆኑ፣ ከዚህ የቤተ ክርስቲያን ስርዓት ውጪ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ቤተመቅደስ መግባት፡- ሴት በወር አበባዋ ጊዜ የምትከለከለው ነገር ቤተመቅደስ መግባትን ነው፡፡ይህም የሆነው በርኩሰት ምክንያት ወይም በኦሪት ሕግ ምክንያት ሳይሆን በቤተመቅደስ መፍሰስ ያለበት ደም አማናዊ የሆነው የክርስቶስ ደም ብቻ በመሆኑ ነው!ይህ ስርዓት ለሴቶች ብቻ ሳይሆን ለወንዶችም ነው፡፡ አንድ ወንድ እየነሰረው ወይም የሆነ ነገር አካሉን ቆርጦት ደም እየፈሰሰው ከሆነ ወደ ቤተ መቅደስ መግባት የለበትም!ምክንያቱም በቤተ መቅደስ ክርስቶስ ደም ውጪ ሌላ ነገር መፍሰስ ስለሌለበት ነው፡፡ **በወር አበባ ላይ ሳለች ሴት ወደ ቤተመቅደስ አትግባ ማለት ቤተ ክርስቲያን አትሂድ ማለት ሳይሆን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄዳ የመጀመሪያውን ቅጽር (አጥር) ከገባች በኋላ በመጠለያ ውስጥ በመሆን ትጸልይ፣ ትማር ወይም ማንኛውንም አይነት መንፈሳዊ ስራዎችን ሰርታ ትመለስ ማለት ነው፡፡ ከመቁረብ፡- ሴቶች ከወር አበባ ሳይነጹ ሥጋ ወደሙ መቀበል አይችሉም፡፡ ይህንን ስርዓት ተላልፈው ወደ ሥጋ ወደሙ እንዲቀርቡ ያደረገ ዲያቆንም ይሁን ቄስ ከክህነቱ እንዲሻር ፍትሕ ነገስት ይደነግጋል፡፡ከግዳጅዋ ያልነጻችውን ሴት በደሟ ወራት ከቤተ ክርስቲያን አግብቶ ሥጋውን ደሙን ያቀበለ ከክህነቱ ይሻር፡፡ፍትነገ 6 ዘሌ 719 ይህ ሥርዓት በሴቶች ላይ ብቻ ሳይሆን ወንዶችም ህልመ ለሊት በሚያጋጥማቸው ሰዓት እንዳይገቡ ይከለከላል፡፡ ቤተ ክርስቲያን የገነት ምሳሌ ናት፡፡ ሔዋን ከአዳም ጋር በገነት ለሰባት ዓመታት ስትኖር የወር አበባ አታይም ነበር፡፡ ቤተ መቅደስ የገነት ምሳሌ መሆኗ የተሟላ እንዲሆን የወር አበባ የምታይ ሴት ወደ ቤተ መቅደስ አትገባም፡፡ 
ይህን የእናት ቤተክርስቲያን ትምህርት ለሌሎቹም እህቶቻችን ሼር በማድረግ እናካፍላቸው፡፡

Comments

Post a Comment